
የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢኖቬሽን ቢሮ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በቴፒ ከተማ የ2018 በጀት ዓመት 6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
የገጠር ኢንዱስትራላዜሽን ሥራ ማጠናከር ፣ የዘርፉ ክፍተቶችን በማረም ለኢንዱስትሪ ሽግግር ፣ አዲስ በማቋቋም ረገድ፣ ነባሩን ኢንዱስትሪ ለማጠናከር በትኩረት ልሰራ አንደሚገባ የቢሮ ምክትል ሀላፊና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ ብርቅነሽ ሻንቆ ተናግረዋል።

በአካባቢ ምርቶች ላይ እሴቶችን ጨምሮ ከመስራት አንጻር ትኩረት ልደረግ አንደሚገባና በቀጣይም ክልሉ የራሱን የሊዝ ፋይናንስ እንዲያቋቁም ሁሉም በቅንጅት ሊሠራ ይገባል።



በተለይም እንደ ሀገር እየተሠሩ ያሉ የ5 ሚልዮን ኮደርስ ሥልጠና እና የዲጂታል መታወቂያ ኢንሼቲቭ ሙሉ በሙሉ እንዲሳካ በትጋት በመሥራት በቀሪ 6 ወራት መሥራት መፈጸም እንደሚገባ የተናገሩት ደግሞ የቢሮዉ ምክትል ሀላፊና የኢኖቬሽን ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስፋዉ ናቸዉ ።
የመንግስት አገልግሎችን ከማዘመን አንጻር ትኩረት ልደረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
ተሳታፊዎቹም በበኩላቸዉ በኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ዘርፍ ቀድሞ የነበሩ ተግዳሮቶች ታርሞ አሁን ወደ ተግባራት መገባቱን አንስተዉ የኢኖቬሽንና በኢንዱስትሪ ሽግግር ዙሪያ አሁንም ከባለድርሻ አካላት በትኩረት በጋራ በመግባባት አንደሚሠሩ ጠቁመዋል።
ተሳታፊዎቹ አክለዉም በቀጣይ የሚቀርቡ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶች ወጥነት እንዲኖራቸዉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አንደሚገባ፣ በታችኛዉ መዋቅር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር መልካም የሥራ ግንኙነቶችን መፍጠር እንደሚገባ አንስተዋል።
በቀጣይም በኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ዘርፍ የተሻለ ዉጤት እንዲመዘገብ ሁሉም ትኩረት ሰጥቶ ተናቦ መስራት እንዳለበትም ተናግረዋል።
በተለይም የኢንዱስትሪ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ መንግስታዊ ድጋፍ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።
በማጠቃላያዉ የቢሮው ሀላፊ አቶ ዘመድኩን ሰለሞን በአዳዲስ ኢንዱስትሪ ከማቋቋም አንጻር የተጀማመረዉን በማስፋት በሁሉም ዞኖች በትኩረት መስራት አንደሚገባ አሳስበዋል።
በኢንዱስትሪ ሽግግር ላይም በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
በገጠሩ ኢንዱስትሪ ተግባር ላይ በቀጣይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ እና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ባዛር ዝግጅት ትኩረት መደረግ እንዳለበትም አሳስበዉ በዞን ደረጃ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በቅርቡ ለማስጀመር ትኩረት እንዲሰጥም አሳስበዋል ሲል ማሻ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
