
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ለቤንች ማጂ ልማት ማሕበር ባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎች የኢትዮ የኮደርስ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል ፦
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ ኃላፊ ዘመድኩን ሰለሞን (ረ/ፕ/ር) እንደተናገሩት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 አካል የሆነው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና እንደ ሀገር የዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በክልሉ ከ18 ሺ በላይ ሰዎች ስልጠናውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።



የ5 ሚሊዮን ኮደርስ የመንግሥት ኢንሼቲቭ መሆኑን ገልፀው ሠልጣኞች የመንግሥት አገልግሎት አሠጣጥ የተሳለጠ እንዲሆን የራሳቸውን ሚና ይጫወታሉ ሲሉ ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም በዚህ ዘርፍ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ባከናወነችው ተግባር ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን ማፍራት ለነገ የማይባል ተግባር በመሆኑ የኢትዮ – ኮደርስ ሥልጠና አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
የሚዛን- ቴፒ ዩኒቨርስቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተረፈ ጌታቸው በበኩላቸው ኮደርስ ሥልጠና ዲጂታል ክሕሎትን እንደሚያሳድግ ጠቁመው የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ ለመረዳት እንደሚያግዝ ተናግረዋል። ስልጠናው ለተማሪዎች ቀጣይ ህይወት አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል።

ተማሪ መሱድ መሃመድ እና ተማሪ በእምነት ጌታሁን በአዳሪ ትምህርት ቤቱ የ12’ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆኑ ኮደርስ ስልጠና በክህሎት እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ተተኪ ትውልድ በመሆናቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል።



ስልጠናው በዌብ ፕሮግራሚንግ ፣ አንድሮይድ ማበልፀግ ፣ ዳታ ሳይንስ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ለተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ታውቋል ሲል የዘገበው (ቤ.ሸ.ቴ) ነው።
